Wintana Aynalem is a young scholar from Ethiopia, currently undertaking an MA in Critical Media and Cultural Studies at SOAS University of London. She has a BA in Political Science and International Relations from Addis Ababa University and is interested in Socio-political research around contemporary issues in Sub-Saharan and East Africa.

Wintana Aynalem, SOAS University of London

Multilingual Locals and Significant Geographies (MULOSIGE)፡ ለዓለም ሥነ-ፅሁፍ አዲስ አቀራራብ በርካታ የሆኑትንና በአብዛኛው ጊዜ የተከፋፈሉትን የሥነ-ፅሁፍ ዓለማትን ‘ከብዙ-ቋንቋ ማህበረሰቦች’ አንፃር ይቃኛል

በሰሜን ህንድ፣ መግረብ እና አፍሪቃ ቀንድ አካባቢ ያሉ ስፍራዎች ካሏቸው ቅድመ ቅኝ-ግዛት የፅሁፍ እና የቃል ልምዶች፤ እንዲሁም ካሳለፉት የብሄራዊ ስርዓት እና የቅኝ-ግዛት ተሞክሮ የተነሳ ለዚህ ፕሮጀክት ተመርጠዋል። ፕሮጀክቱ በሶስት ወቅቶች ላይ ያተኩራል-የቅኝ አገዛዝ ማጠናከሪያ፣ ዲሲኖኒዜሽን እና አሁን ያለው ዓለም አቀፋዊ ጊዜ። በመቀጣል ፕሮጀክቱ ስለ ባህላዊ ውስጣዊ ትስስሮች፣ በአለም ሥነ-ጽሑፍ ላይ የአገሬው ተወላጅ ክርክሮች፣ አንጋፋና እና አዳዲስ የብዙ-ቋንቋ-ቃላት፣ እንዲሁም የህትመት እና የቃል አቀንቃኞች እና ቴክኖሎጂዎችን ይዳስሳል።

የዓለም ሥነ-ፅሁፍን መታወቂያነት ከእንግሊዘኛ ቋንቋ አመለካከት አንፃር የሚያደርግን አስተሳሰብ ግብረ-መልስ መስጠት ‘የብዙ ቋንቋዊ አካባቢዎችና ወሳኝ ስፍራዎች’ (MULOSIGE) ዋና ዓላማ ነው። ይህም ብዙ-ቋንቋዊነትንና የክልላዊ እንዲሁም የሽግግር ፅሁፋዊ መስኮች ላይ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ በርካታ ምክንያቶችን በማጉላት የዓለም የሥነ-ጽሑፍ አቀራረብን በእንግሊዘኛ ለመለየት ይጥራል፤ በተጨማሪም ከማስመሰል እና ከማሰራጨት ይልቅ የመዋዋስ እና የፈጠራ ችሎታ ላይ ትኩረት ያደርጋል።

ባለን መረጃ መሠረት በሰሜን ህንድ፣ ሞሮኮ እና ኢትዮጲያ መካከል ቀጥተኛ ፅሁፋዊ ተያያዥነት የለም። በዚህም ምክንያት ፕሮጀክቱ ከቁጥጥር ዞኖች ወይም ግንኙነቶች ይልቅ ንድፍ እና ማነፃፀር ላይ ያውጠነጥናል። የዓለምአቀፍ ዝውውርን ወቅታዊ አቀራረብ የሚያሟላ አካባቢያዊ የዓለም ሥነ-ፅሁፍ ጥናት  ዓላማን ለማሳካት ማነፃፀር ቁልፍ መሳሪያ ነው። በተጨማሪም የአውሮጳን ማዕከላዊ አድርጎ የእስያ እና አፍሪቃን መዳረሻ ላይ የሚያስቀምጥን ቀለል ያለ እና አሳሳች አስተሳሰብን ይለውጣል::

የአካባቢያዊ የብዙ-ቋንቋዊነት አቀራረብ “የዓለም ክልሎች አውሮጳን ማዕከል ባደረገ የዓለም-ሥርዐት ተተክተዋል” ከሚል ታሪካዊ ግንዛቤ ጋር ይፃረራል:: በዚህም ረገድ ዓላማው የባህል ሽግግርና የመበዳደር አስተሳሰብን ለሥነ-ፅሁፍ ዕድገት እና ፍሬአማነት መዋጮ አድርጎ ማቅረብ ነው:: በተያያዥነት ይህ ‘የንጉሠ ነገሥቱ ማዕከላዊ ቅኝ ግዛት’ ዘንግ አንድ ክፋይ በአንድ ሞዴል ውስጥ ብቻ ነበር እናም የአውሮጳውያኑ ሥነ-ጽሑፍ በዚህ ጐርፍ ተጠቃለዋል።

ዓላማው ባለ ‘ብዙ-ቋንቋ አካባቢዎች እና ወሳኝ ቦታዎች’ ለዓለም ዓቀፍ ሥነ-ፅሑፍ ጥናት (የአውሮጳንም ጨምሮ) ተስማሚ ናቸው የሚለውን መደገፍ ነዉ። ይህም የዓለም የሥነ-ፅሑፍ የመስክ ዘዴዎችን፣ የስልጠና ሞዴሎችን፣ ተጨባጭ የሆነ የሥ-፡ፅሁፍ አጠናን፣ መልመጃዎችን እንዲሁም የተለያዩ ቋንቋዎች ላይ ተመርኩዞ የዓለምን የሥነ-ፅሁፍ ታሪክ  ይበልጥ መረዳት እንደምንችል ያስረዳል። በተጨማሪም ፕሮጀክቱ ከአውሮጳ, እንግሊዝ እና ከተለያዪ ቦታዎች ከተውጣጡ ምሁራን ጋር የውይይት መድረክ በመክፈት ጉዳይ ላይ ተመካከሯል።

ጥናቱ በቀዳሚነት የሚመራው በፕሮፌሰር ፍራቼስካ ኦርሲኒ እና ከSOAS
ዩኒቨርሲቲ በተወጣጡ የተመራማሪዎች ቡድን ነው። እነኝህም: ዶ/ር ከሪማ ላችሂር፣ ዶ/ር  ሳራ ማርዛጎራ፣ ዶ/ር ፋቲማ በርኒ፣ ዶ/ር ዒትዘኣ ጎኢኮሊኣ-ዓሚኣኖ፣ ጁላይ ብላላክ፣ ጃክ ክሊፍት እና አየለ ከበደ ሮባ ናቸው። የዓለምን አንገብጋቢ ጥያቄዎች እና ዉይይቶችን በጣልቃ ገብነት አመለካከትን ማስፋት አንደ ግቡ አድርጎ የያዘዉ የባህል የሥነፅሁፍ እና የድህረ ቅኝ ግዛት ምርምር ማዕከል (Centere for Cultural, Literary and Postcolonial studies) የዚህ MULOSIGE ፕሮጀክት ዋና አስተናጋጅ ነዉ።  ፕሮጀክቱ ለ፭ ዐመት ሚዘልቅ ሲሆን እ.አ.አ ታህሳስ ፪፲፻፳ ይጠናቀቃል፤ በዚህ ጊዜ የተለያዩ ዝግጅቶች በSOAS እና አዉሮጳ፣ ሞሮኮ፣ ኢትዮጲያ እና ሰሜን ህንድ በሚገኙ ባልደረባ ተቇማት ይካሄዳሉ።

ከላይ በተጠቀሱት ሦሥት የጉዳይ ጥናቶች መሰረት ፕሮጀክቱ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ይጠይቃል፡

 • በእያንዳንዱ ክልል እና በእያንዳንዱ ቋንቋ ውስጥ አንጋፋ ‘ወሳኝ ስፍራዎች’ ምን ነበሩ?
 • እነሱ እርስ በርስ ይገጣጠሙ ነበር ወይስ ተለያዩ?
 • በቅኝ አገዛዝ ቅደም ተከተል ላይ, “አለም አቀፋዊ ሥነ-ጽሑፍ” እና በዚህ “የዓለም ሥነ-ጽሑፍ” ዘመን ምን አዲስ ‘ወሳኝ ስፍራዎች’ አሉ?
 • እንዴት ነው ስለ የአካባቢ እና የሽጝር የፅሁፍ ቦታዎችን ከቀላል ቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ገደብ ወጥተን፤ የታሪክ ብዝሃነትንና የከተማ ዙሪያ እንዲሁም አካባቢያዊ የጋራ መግባባትን በሚያንፀባርቅ መልኩ ማሠብ የምንችለው?
 • በሰሜን ህንድ፣ ሞሮኮ እና ኢትዮጵያ ያሉ ዘመናዊ ጸሐፊዎች ከአንዳንድ አንጋፋ አጻጻፎች፨ዘውጎች እና ከሌሎች  ሥነፅሁፎች የተዋሷቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?
 • እንዴት እና በምን መልኩ የባህል ሽግግር እና ውሰት ተካሄደ?
 • አካባቢያዊ የዓለም ሥነ ፅሑፍ ክርክሮች ምን ይመስሉ ነበር፣ የትኛውን አከበሩ ለየትኛውስ ልዩ መብት ሰጡ ፣ እና ለምን?
 • ዘመናዊው የቋንቋ፡ፅሑፋዊ ምሥረታ ያገለለዉ ምንድንን ነዉ?
 • እንዲሁም በህትመትና በሌሎች ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ላይ ጥንታዊ ተዋናዮችና አዕምሮዎች እንዴት ኖረዋል? ምን ዓይነት የተቀናበሩ የቃል-የፅሁፍ/የታተሙ ቅጾችንስ አሳድገዋል?
 • የእነዚህ ‘ብዙ-ቋንቋዎች አካባቢዎች’ ተለዋዋጭ መለያ ምን ነበር ምንስ ነው?
 • ሰዎች ከአንድ በላይ ቋንቋዎች ያንባሉ እና ይፅፋሉ፧ ወይስ አንዱን ያንባሉ እና ይፅፋሉ፣ ከዚያ በሌሎች ውስጥም ይሳተፋሉ?
 • በተለያዩ ቋንቋዎች የሥነ፡ጽሑፍ ምርጫዎች ይለያሉ ወይ ይቀላቅላሉ?
 • ማሰብ ያለብን በንባባዊ፣ በፅሑፋዊ፣ እና ፀሀፊያዊ እውቀቶች አንፃር ነው፣ ወይንስ ካለመኖራቸዉ?
 • በብዙ-ቋንቋዎች የተደረጉ ጽሑፋዊ ምርቶች ዓለም አቀፍ እውቅና አግኝተዋል፣ እና ከሆነስ እንዴት?
 • በእነዚህ የፅሑፍ መስኮች ውስጥ ያለዉ የአለምአቀፍ ሥርጭት ውስጣዊ ሥርጭት ጋር ምን ያህል ይመሳሰላል?

ጉዳይ ጥናቶች

የሰሜን ህንድ፣ የመግረብ እና የአፍሪካ ቀንድ ክልሎች የኘሮጀክቱን የጉዳይ ጥናቶች ያጠቃልላሉ። ፣ ፤